WELCOME TO ETHIOPIAN CONSTRUCTION AUTHORITY

ለተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ስልጠና ተሰጠ

ለተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ስልጠና ተሰጠ

ለተቋሙ የስራ ኃላፊዎች በአካል ጉዳተኞችና ኤችአይቪ/ኤድስ ማካተት ጉዳይ ላይ ስልጠና ተሰጠ
መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም
***********
በኤች አይቪ ኤድስና አካል ጉዳተኞችን አካቶ በመስራት አስፈላጊነትና የሕግ ማዕቀፎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ለኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን አመራሮችና የስራ ሃላፊዎች መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በስልጠናው መክፈቻ ስነስርዓት ላይ የኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ማተቤ አዲስ እንደገለፁት ክህሎትና እውቀትን ለመጨመር ታሳቢ ተደርገው የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ ግንዛቤን በመፍጠር በሙያዊ ተልእኮዎች ላይ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል፡፡
በተለያዩ ሴክተሮች የሚወጡና ከኮንስትራክሽን ስራዎች ጋር ተዛምዶ ያላቸውን ህጎችን በመገንዘብ ተፈጻሚ ማድረግ ላይ ትኩረት መሰጠት አለበት ብለዋል፡፡
በዋናነትም በግንባታ ሂደቶች ላይ ተፈፃሚ መሆን ያለባቸው በሴቶችና በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ የሚወጡ ህጎችን ማስፈጸምና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም አቶ ማተቤ አዲስ አስገንዝበዋል ፡፡
አያይዘውም በቀጣይ ተቋሙ ጠንካራ ተልእኮዎች እንደሚኖሩት አውስተው ተልዕኮውን በብቃት ለመወጣት በእውቀት፣ በክህሎት እና በአመለካከት ዝግጁ መሆን እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
ስልጠናው በዋነኝነት ትኩረት ያደረገው ተቋሙ በሚያከናውናቸው ተግባራት ውስጥ የአካል ጉዳተኞችን ጉዳይና የኤችአይቪ ኤድስ ጉዳይን በማካተትና በተለይም በሚሰራው የቁጥጥር ተግባር ትኩረት በመስጠት እንዲሰራ ተሳቢ ተደርጎ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ተቋማት አካል ጉዳተኞችን አካቶ መስራት በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ አሳልፈው አመዲን ስልጠና ሰተዋል፡፡
በተ.መ.ድ የአካል ጉዳተኞች ኮንቬንሽን በተቀመጠው መሰረት አካል ጉዳተኛ ማለት በግለሰብ ላይ በደረሰበ የአካል ፣የአዕምሮ፣ የስሜት ህዋሳት ጉዳትን ተከትሎ የሚመጣ የኢኮኖሚ ፣ የማህበራዊ፣ የፖለቲካዊ ወይም የባህላዊ መድልኦ ሳቢያ የእኩል ዕድል ተጠቃሚና ተሳታፊ ያልሆነ ሰው ማለት መሆኑን የገለጹት አሰልጣኙ የኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ከሚሰራቸው የዲዛይን የግንባታ ሂደቶች ቁጥጥር ላይ በትኩረት አካል ጉዳተኞችን አሳታፊ ነው ብሎ መገምገም እና ቁጥጥር ማድረግ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም አካል ጉዳተኞች ከሌላው ሰው የሚለዩት አካል ጉዳት በደረሰባቸው ጉዳይ ላይ እንጂ በሌሎች ተሳትፎዎች ባለመሆኑ አሳታፊ ያደረገ ስራ መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
በተለይም አካል ጉዳተኞችን አካታችና ተጠቃሚ የማድረግ ስራዎችን ተፈፃሚነት የሚያረጋግጥ፣ ችግሮችን የሚቀርፍ እና የተጠያቂነትን ስርዓት እውን የሚያደርግ ህግ እየተዘጋጀ ሲሆን ተጠናቅቆ ከፀደቀ በኋላ በ2014 ተግባራዊ እንደሚደረግም ገልፀዋል፡፡
የስልጠናው ሁለተኛ መርሃ ግብር ላይ ኤችአይቪ/ ኤይድስን የመከላከል ስራን አካታች በማድረግ ዙሪያ ላይ ሲሆን ከኤች አይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት በአቶ ክፍሌ ምትኩ ተሰጥቷል፡፡
ዓለም አቀፍ ገፅታውን አስመልክቶ በሰጡት መረጃ ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ በኤችአይቪ/ኤድስ ምክንያት 32 ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸውን አጥዋል፣ 37.9 ሚሊዮን ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል፣ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰዎች በየአመቱ በቫይረሱ ይያዛሉ እንዲሁም በየአመቱ 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሰዎች ለሕልፈተ ሕይወት ይዳረጋሉ፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃም የቫይረሱ ስርጭት በወረርሽኝ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑን የገለፁት አቶ ክፍሌ ምትኩ፣ በማህበረሰቡም ሆነ በተቋማት ዘንድ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የመከላከል ስራው መጠናከር አለበት ብለዋል፡፡
እንደ ኮንስትራክሽን ሴክተር ሰፋፊ ፕሮጀክቶች የሚከናወኑ እንዲሁም ከፍተኛ የሰው ኃል የሚሰማራበት ሴክተር ከመሆኑም አንፃር የተቀናጀ፣ የተናበበ፣ ተከታታይነት ያለው የመከላከል ስራ መከናወን እንዳለበትም ተመልክቷል፡፡
በስልጠና ርዕሶቹ ላይ ከተሳታፊዎች አስተያይቶች እና ግብረመልሶች ተሰጥተዋል፡፡
ንግስት ፍስሃጽዮን
ቢሾፍቱ ከተማ

Leave Your Comment

Bole, Addis Ababa,Ethiopia

Opening Hours:

Mon – Fri: 8:00 am – 6:00 pm

Calander

October 2024
M T W T F S S
 123456
78910111213
14151617181920
21222324252627
28293031  

ECA News & Updates

The latest Ethiopian Construction Authority news, articles, and resources, sent straight to your inbox every month.

Ethiopian Construction Authority © 2020. All Rights Reserved
Designed & Developed by Kanenus Technologies 0973200216