የኢኮባ ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽንታህሳስ 12 ቀን 2014 ዓ.ም***********የሰው ልጅ ደህንነትና ጤንነት መጠበቅ ሕጋዊ ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊ መብት ነው፡፡ ይህ መርህ በግንባታ ስራ ላይም ዕውን ይሆን ዘንድ የተለያዩ የሕግ ድንጋጌዎች እንዳሉም ይታወቃል፡፡ እንዲያም ሆኖ ግንባታ የደህንነትና የጤንነት ስጋት ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ በዚህም ምክንያት በርካታ ዜጎች እና የግንባታ ሙያተኞች ለከባድ አደጋ፣ ለአልጋ ቁራኛ እንዲሁም ለሞት ተዳርገዋል፡፡ አስከፊ ገፅታ የሆነው የግንባታ ስራ ላይ አደጋ ጥቂት መንስዔዎችን እንመልከት፡፡ 1. በግንባታ አካባቢው ምክንያት • የግንባታ ግብዓቶች ጥራት መጓደል• የመገልገያ ትጥቆችና መሳሪዎች አለመሟላት• የስራው አካባቢ በቂ ብርሃን አለመኖር• የስራ ቦታዉ ከፍተኛ ሙቀት ወይም ቅዝቃዜ መኖር• የስራ አካባቢው አቧራማ፣ የተዝረከረከ እና ቆሻሻ መሆን• አደጋ ላይ የሚጥል ከባድ ድምፅ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡2. በሰዎች ምክንያት እንደመረጃዎች ከሆነ በሀገራችን ዘጠና አምስት በመቶ የሚሆኑት የግንባታ አካባቢ አደጋዎች በሰዎች ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው፡፡ ዋና ዋናዎቹም፡-• የጥንቃቄ ጉድለት• ድካምና መዛል • ያልተገባ ጥድፊያ• ሕጎችን ያለማክበር• ደባል ሱስ• ቸልተኝነት• የግንዛቤ እጥረት• ኃላፊነትን በአግባቡ አለመወጣት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የግንባታ ባለድርሻ አካላት ሁሉ በቁርጠኝነት፣ በትጋት፣ በቅንነት፣ በአስተዋይነት፣ በጥበብ፣ እንዲሁም ለሕጎች ተገዥ በመሆን ኃላፊነትን እና ሙያዊ ስነምግባርን መወጣት ይገባል፡፡ የደህንነትና የጤንነት ሕጎችን ሕብር ፈጥሮ መተግበር ከተቻለ፣ ጥንቃቄን እንደ እምነት አጥብቆ ከተያዘ የግንባታ ፕሮጀክቶች የስራ ላይ ደህንነት ስጋቶችን ማስወገድ ይቻላል፡፡ ይህ ሲሆን ከሀብቶች ሁሉ የላቀው ሀብት የሆነው ሰው ዕድሜው አያጥርም፣ ሩቅ አልሞ በአጭር አይቀርም፣ ግዙፍ ሃሳቡ አይሰናከልም፡፡ ይልቁንም ለሀገራዊ ማህበረ-ኢኮኖሚ ከፍታ እንደ አሳንሰር ለሚቆጠረው የግንባታው ዘርፍ ልዕልና ወርቃማ አስተዋፅዖ እንዲያበረክት ያስችለዋል፡፡እናም ገንቢዎች፣ አስገንቢዎች፣ የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች፣ አማካሪዎች፣ መሐንዲሶች፣ ግብኣት አቅራቢዎች፣ ሕግ አውጪዎችና አስፈፃሚዎች እንዲሁም ሌሎች የግንባታ ባለድርሻ አካሎች ለግንባታ የስራ ላያ ደህንነትና ጤንነት መጠበቅ ልዩ ትኩረት አድርጎ በጋራ መረባረብ ይገባል፤፡
17You and 16 others2 Comments5 SharesLikeCommentShare