የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን( ኢኮባ) አመራሮችና ሰራተኞች የዛፍ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

(ኢኮባ ነሐሴ 16 ቀን 2015 ኣ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን( ኢኮባ) አመራሮችና ሰራተኞች ነሐሴ 17 ቀን 2015 ዓ.ም የዛፍ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡
በየካ ክ/ከተማ ሚሊኒየም ፓርክ ላይ በተካሄደው ፕሮግራም ላይ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች 1500( አንድ ሺህ አምስት መቶ የዛፍ ችግኞችን ተክለዋል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ ባስተላላፉት መልዕክት የዕለቱ ክንውን በሀገር አቀፍ ደረጃ “ነገን ዛሬ እንትከል”በሚል መርህ ኢትዮጵያን በአረንጓዴ እፅዋት የማልበስ ታላቅ ሀገራዊ ተልዕኮ አካል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በምስራቁ እና በምዕራቡ ዓለም በሚገኙ ሀገሮች ላይ የተከሰቱት ሰሞነኛ የተፈጥሮ አደጋዎችን በዋቤነት የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ ዋነኛው መንስዔው ከአየር ንብረት መዛባት ጋር የተያያዘ መሆኑንም አውስተዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ያለው የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻም በኣለም ደረጃ ስጋት እየሆነ የመጣውን የአየር ንብረት መዛባትና ይህንኑ ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የአደጋ ስጋቶችን በማስወገድ ረገድ የኢትዮጵያን ሚና ከፍ የሚያደርገው እንደሆነም ኢ/ር መስፍን ነገዎ ገልፀዋል፡፡
በተቋም ደረጃ ለአምስተኛ ጊዜ በመርሃ ግብሩ ተሳትፎ መደረጉን አውስተው ይህን ቅዱስ አላማ ባህል በማድረግ ለትውልድ ማሸጋገር ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ መንግስት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን( ኢኮባ) ም/ዋና ዳይሬክተሮች አድርጎ በቅርቡ የሾማቸው አመራሮች ከሰራተኛው ጋር ትውውቅ አድርገዋል፡፡
ኢ/ር ደረጀ አረጋኸኝ በኢኮባ የግንባታዎች ቁጥጥር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር፤ ዶ/ር ሙአዝ በድሩ በኢኮባ የምዝገባና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሾማቸው ይታወቃል፡፡

የኢኮባ ህዝብግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን

https://t.me/Ethiopiaconstructionaouthority/620

https://www.facebook.com/oficialpageofECA/

https://www.youtube.com/channel/UCUJNzKAbrJzNV9w3rJwc4tg

Previous በ2016 በጀት አመት የተቋም ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ የሱፐርቪዥን ስራ ተካሄደ

Leave Your Comment

Connect With Us

Bole, Addis Ababa,Ethiopia

Mon – Fri: 8:00 am – 6:00 pm

Calander

January 2025
M T W T F S S
 12345
6789101112
13141516171819
20212223242526
2728293031  

Useful Links

ECA News & Updates

The latest Ethiopian Construction Authority news, articles, and resources, sent straight to your inbox every month.

Ethiopian Construction Authority © 2020. All Rights Reserved
Designed & Developed by Kanenus Technologies 0973200216