የመልካም አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እና የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡


(ነሀሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም )፡- የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የመልካም አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እና የመፍትሄ ሃሳቦች ሰነድ ላይ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል፡፡
የመልካም አገልግሎት መስፈን ለሀገራዊ ማህበረ ኢኮኖሚ ዕድገት የሚጫወተው ሚና የላቀ በመሆኑ በዚህ ረገድ እንደየተቋማት ተጨባጭ ሁኔታ የታዩ በጎ ገፅታዎች የመኖራቸውን ያህል ችግሮችም መስተዋላቸው ተመልክቷል፡፡
ሀገራዊ የልማትእቅዶችን ለማሳካት እና የሪፎርም ስራዎችን በውጤታማነት ለመተግበር የመልካም አገልግሎትን ማስፈን ወሳኝ መሆኑ እና መገለጫዎቹ ተብራርተዋል፡፡
በየተቋማቱ የአገልግሎት አቅርቦት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችና መንስዔዎቻቸው እንዲሁም መፍትሄዎች ላይም ገለፃ ተሰጥቷል፡፡
የጥቅም ትስስር፣ አድልኦና በደል፣ የህጎች እና አሰራሮች ጥሰት፣ በጥፋት ልክ ተጠያቂነት አለመኖር፣ የብቃት ቸግር ፣ የተነሳሽነት አለመኖር በአገልግሎት ጥራት መጓደል እና ይህንኑ ተከትሎም በሀገር ማህበረ-ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ እያሳደረ የሚገኘው አሉታዊ ተፅዕኖዎችም በሰፊዉ ተብራርተዋል፡፡
የሰነዱን ማብራሪያ ተከትሎም ከተሳታፊዎች እንደሀገር ብሎም እንደተቋም እና እንደግለሰብ በአገልግሎት ረገድ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የተመለከቱ አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡
የአገልግሎት ጥራት መጓደል በሀገር ላይ የመልካም አስተዳደር ችግር ዋነኛ መንስዔ ስለመሆኑ ተሰምሮበታል፡፡
በተቋም ደረጃ የምዝገባ አገልግሎት አሰጣጡን ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋ እና የተገልጋዩን ጊዜ ቆጣቢ ለማድረግ ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት ዝርጋታው ላይ የተጀመሩ ጥረቶች ይበልጥ መሻሻል እንዳለባቸውም ግብረመልስ ሰጥተዋል፡፡
እንደተቋም ህዝብ የሚጠብቀውን ጥራት ያለው የግንባታ አገልግሎት እውን በማድረግ ረገድ የቁጥጥር ስራዎች በዚህ አውድ የተቃኙ መደረግ እንዳለባቸውም ተመልክቷል፡፡
በተጨማሪም በየደረጃው የሚገኘው አመራር ሁለንተናዊ አርአያ በመሆን ለአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ሚና መጫወት ይገባዋል ተብሏል፡፡
በዋናነትም የውሳኔዎች መዘግየት በአገልግሎት ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድሩ በመገንዘብ በዚህ ረገድ ልዩ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
በየደረጃው ያለው ሰራተኛም በአመለካከት፣ በክህሎት እና በዕውቀት በመታነፅ ተገልጋይን በክብርና በቅልጥፍና በማስተናገድ ጥራት ያለው አገልግሎትን እውን ማድረግ እንደሚገባቸውም ተመልክቷል፡፡
የሙስና እና የሌብነት ተግባራት መስፋፋት፣ የአገልጋዩ ነባራዊ የኑሮ ሁኔታ፣ በብልሹ አሰራሮች ላይ የተጠያቂነት ስርዓት አለመጠናከር፣ የህጎችና መመሪያዎች ጥሰት ለአገልግሎት ጥራት መጓደል እና በዚህም ምክንያት ለሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መንስዔዎች በመሆናቸው ከመንግስት ጀምሮ በየደረጃው እስከህዝብ ድረስ ቁርጠኛ የለውጥ ተግባራትን ማከናወን አለባቸው ሲሉም አስተያየት ሰጪዎች አስገንዝበዋል፡፡

የኢኮባ ሕዝብግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ ፡- https://www.facebook.com/oficialpageofECA/
ቴሌግራም፡- https://t.me/Ethiopiaconstructionaouthority
ዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCUJNzKAbrJzNV9w3rJwc4tg
Ethiopian construction authority
ዌብሳይት፡- www.eca.gov.et

Previous ኢኮባ አመራሮች እና ሰራተኞች በሀገራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ አፈፃፀም እና ቀጣይ ዕቅድ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡

Leave Your Comment

Connect With Us

Bole, Addis Ababa,Ethiopia

Mon – Fri: 8:00 am – 6:00 pm

Calander

December 2024
M T W T F S S
 1
2345678
9101112131415
16171819202122
23242526272829
3031  

Useful Links

ECA News & Updates

The latest Ethiopian Construction Authority news, articles, and resources, sent straight to your inbox every month.

Ethiopian Construction Authority © 2020. All Rights Reserved
Designed & Developed by Kanenus Technologies 0973200216