የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች ተገልጋዮችን በማስተናገድ ላይ ናቸው፡፡

በስነ-ምግባር የታነፀ አገልግሎት ክብር ነው !
(ጳጉሜን 1 ቀን 2015 ዓ.ም)፡-በሕግ አካባሪነት ጥበብ የተቃኘ አገልግሎት፣ በአወንታዊ አመለካከት ጥራት የታጀበ አገልግሎት፤ በስራ አፍቃሪነት ባህል የተተገበረ አገልግሎት፤ ስነ-ምግባርንና መልካም ስብዕናን ከተላበሰ ልቦና የፈለቀ አገልግሎት ሰው የመሆን መገለጫዎች ናቸው፡፡ የክብር፣ የስብዕና፣ የቅንነት፣ የአስተዋይነት፣ የብስለት መገለጫዎች ናቸው፡፡
በትህትና የተሞላ አገልግሎት ክብር ነው፡፡ በአገልግሎት ላይ የሚፈልቁ ትሁት ቃላት ቀላል እና አጭር ጊዜን የሚወስዱ ናቸው፡፡ መዓዛ ጠረናቸው ግን በሰፊው የሚናኝ ነው፡፡ ጥዑም ድምፃቸው አድማስ ተሻጋሪ የሆነ የድምፅ ሞገድ ነው፡፡
አገልግሎት አሰጣጣችን የእኛነታችን ስብዕና መለኪያ ሚዛን ጭምር ነው ፡፡ መልካም ስነምግባር ግርማ ሞገስ ነው፡፡ ስብዕናን እንደ አልማዝ የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ የጤናማ ግንኙነት ቁልፍ ነው ፡፡ የሚያረካ አገልግሎት ከመልካም ግንኙነት፣ ከክብር፣ ከፍቅር፣ ከትህትና፣ ከቅንነት ከፍትሃዊነት ይመነጫል፡፡
የኢኮባ አመራሮችና ሰራተኞች የተሰማራንበት ግዙፍ ዘርፍ ሀገራዊ ፋይዳዉ የላቀ ነው፡፡ በተሰማራንበት ቦታ በስነምግባር የታነፀ አገልግሎት መስጠት ክብር ነው ! ምክንያቱም የተሰማራንበት ኢንዱስትሪ የአገር ምልክት ነው፡፡ የአገር ብልፅግና ነው፡፡
በተሰማራንበት ኢንዱስትሪ ውስጥ ትጋትን የተላበሰ፣ ጤናማ አሰራርንና ግንኙነትን ያሰፈነ፣ ከብልሹ አሰራሮች የጸዳ፣ ወርቃማ አስተሳሰብን ያነገበ አገልግሎት መስጠት ማለት ትውልድንና ሀገርን መውደድ ማለት ነው ፡፡
በእነዚህ ወርቃማና ብርሃናማ አስተሳሰበቦች ቅኝት ውስጥ ሕብር ከፈጠርን ተቋማችን አንፀባራቂ ስኬትን ይቀዳጃል፣ ለኢንዱስትሪው ከፍታ፣ ለሀገር ብልፅግና በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩላችንን ተወጣን ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ጀግንነት ነው ፡፡

የኢኮባ ሕዝብግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ ፡- https://www.facebook.com/oficialpageofECA/
ቴሌግራም፡- https://t.me/Ethiopiaconstructionaouthority
ዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCUJNzKAbrJzNV9w3rJwc4tg
Ethiopian construction authority
ዌብሳይት፡- www.eca.gov.et

Previous የመልካም አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እና የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

Leave Your Comment

Connect With Us

Bole, Addis Ababa,Ethiopia

Mon – Fri: 8:00 am – 6:00 pm

Calander

December 2024
M T W T F S S
 1
2345678
9101112131415
16171819202122
23242526272829
3031  

Useful Links

ECA News & Updates

The latest Ethiopian Construction Authority news, articles, and resources, sent straight to your inbox every month.

Ethiopian Construction Authority © 2020. All Rights Reserved
Designed & Developed by Kanenus Technologies 0973200216