ኢኮባ አመራሮች እና ሰራተኞች በሀገራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ አፈፃፀም እና ቀጣይ ዕቅድ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡

(ኢኮባ፡-ነሐሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም) ለኢኮባ አመራሮች እና ሰራተኞች በሀገራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ አፈፃፀም እና ቀጣይ ዕቅድ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡
ግንዛቤ ማስጨበጫው ሀገራዊ የ10 ዓመት የመጀመሪያው መካከለኛ ዘመን ( 2013-2015 ዓ.ም) ዋና ዋና አፈፃፀም እና የቀጣይ የመካከለኛ ዘመን ( 2016-2018 ዓ.ም) የልማት ዕቅዶች ላይ ያተኮረ ነው፡፡
የኢኮባ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ ባቀረቡት ሰነድ ላይ እንደተመለከተው የልዩ ልዩ ክፍላተ-ኢኮኖሚዎች ዝርዝር የዕቅድ አፈፃፀም እና የቀጣይ መካከለኛ ዘመን ዕቅድ ግቦች ቀርበዋል፡፡
ዓለማቀፍ እና አህጉራዊ ልዩ ልዩ ፈተናዎች ቢደቀኑም ሀገራዊ የመካከለኛ ዘመን ዕቅዱ አፈፃፀም አበረታች እንደነበር ተመልክቷል፡፡
እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን ቀመር በ2023 የወጡ የአለም አቀፍ ተቋማት መረጃዎች እንዳመላከቱት ዓለማቀፍ ተፅዕኖዎች በኢኮኖሚ ላይ የፈጠሩት ግድድር በበርካታ ሀገሮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ቢያስከትልም ኢትዮጵያ ተፅዕኖዎቹን በመቋቋም አወንታዊ ዕድገት እንዳስመዘገበች ኢ/ር መስፍን ነገዎ አብራርተዋል፡፡
ትላልቅ አደጋዎችን በመቋቋም የተመዘገበው የዕድገት ምጣኔ መንግስት በየክፍላተ ኢኮኖሚው ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች እና ትግበራ ስለመሆኑም ማብራሪያ ቀርቧል፡፡
በዚሁ መሰረትም የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የውሃ እና ኢነርጂ፣ የመሰረተ ልማት፣ የአገልግሎት እንዲሁም ሌሎች ከአስር በላይ የሆኑ የኢኮኖሚ ዘርፎች ያስመዘገቧቸው አሃዛዊ የዕቅድ አፈፃፀም ተብራርቷል፡፡
በተያያዘም የኢኮኖሚ ዘርፎች የቀጣይ መካከለኛ ዘመን የልማት እና የኢንቨስትመንት ዕቅድና ተጠባቂ ውጤቶች እንዲሁም ዘርፎቹ የሚጫወቱት ሚና በዝርዝር ቀርበዋል፡፡
በማክሮ ኢኮኖሚ ደረጃ ቀጣይ መካከለኛ ዘመን ዕቅድ ላይ ለየክፍላተ ኢኮኖሚዎች በጠ/ሚኒስትሩ የተሰጡ አቅጣጫዎችም በሰነዱ ላይ ተመላክተዋል፡፡
እንደ ዘርፍ በማክሮ ኢኮኖሚ ደረጃ የመሰረተ ልማትን ማሻሻል እንዲሁም እንደተቋማ ስታንዳርዳይዜሽን ላይ ትኩረትና አቅጣጫ የተሰጣቸው ግቦች ስለመሆናቸው ኢ/ር መስፍን ነገዎ አስምረውበታል ፡፡
ሰራተኛው አጠቃላይ የመካከለኛ ዘመን የዕቅድ አፈፃፀሙ እና የቀጣይ ዕቅዶችን አውድ በመገንዘብ ከተቋማዊ ዕቅድ ጋር አጣጥሞ መረባረብ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
ሰነዱን ተከትሎ ተሳታፊዎች አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡ የዕቅድ ዘመኑ አፈፃፀም እና የቀጣይ ዕቅዶች ላይ ግንዛቤ እንዲፈጠር መደረጉ እንደሀገር የጋራ አስተሳሰብን በማስረፅ እና ሀብትን በማቀናጀት የጋራ ርብርብ ለማድረግ መስፈንጠሪያ ስለመሆኑ ግብረመልስ ቀርቧል፡፡
ከዚህ አንፃርም እንደሴክተር ቅንጅታዊ አሰራር ላይ በማተኮር ርብርብ ማድረግ ተገቢነቱንም አስተያየት ሰጪዎች ገልፀዋል፡፡
ከተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች አንፃር በዕቅዱ ውስጥ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ላይ የመብራሪያ ጥያቄዎችም ቀርበዋል፡፡
ኢ/ር መስፍን ነገዎ በቀረቡ ግብረመልሶች እና ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ለተሳታፊዎች ግንዛቤ አስጨብጠዋል፡፡

የኢኮባ ህዝብግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ ፡- https://www.facebook.com/oficialpageofECA/
ቴሌግራም፡- https://t.me/Ethiopiaconstructionaouthority
ዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCUJNzKAbrJzNV9w3rJwc4tg
Ethiopian construction authority
ዌብሳይት፡- www.eca.gov.et

Previous What is Construction Industry Audit?

Leave Your Comment

Connect With Us

Bole, Addis Ababa,Ethiopia

Mon – Fri: 8:00 am – 6:00 pm

Calander

December 2024
M T W T F S S
 1
2345678
9101112131415
16171819202122
23242526272829
3031  

Useful Links

ECA News & Updates

The latest Ethiopian Construction Authority news, articles, and resources, sent straight to your inbox every month.

Ethiopian Construction Authority © 2020. All Rights Reserved
Designed & Developed by Kanenus Technologies 0973200216