WELCOME TO ETHIOPIAN CONSTRUCTION AUTHORITY

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የመልካም ስራ አፈፃፀም ተሸላሚ ሆነ

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የመልካም ስራ አፈፃፀም ተሸላሚ ሆነ

አቢሲኒያ የኢንዱስትሪ ሽልማት ድርጅት “ትጉኃንን እንሸልማለን” በሚል መሪ ቃል ለ2016 ዓ.ም ባዘጋጀው የሽልማት መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የዳይመንድ ደረጃ የወርቅ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

የሽልማት ድርጅቱ መልካም የስራ አፈፃፀም ያላቸውን የመንግስት እና የግል ተቋማት ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ በኢንተርላግዠሪ ሆቴል ባዘጋጀው ስነስርኣት ሸልሟል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ የዳይመንድ ደረጃ የወርቅ ዋንጫ ሽልማቱን  የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ ከዕለቱ የክብር እንግዳ የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እጅ ተቀብለዋል፡፡

በተጨማሪም የተቋሙ ሶስት ከፍተኛ አመራሮች እና ሰባት ሰራተኞች የ”ትጉኃንን እንሸልማለን” መርሃግብሩ የወርቅ ኒሻን ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

ተቋሙ ለሽልማት የበቃው ባለፉት አምስት አመታት በምዝገባና ስታንዳርዳይዜሽን እንዲሁም በግንባታ ቁጥጥር ዘርፎች ባስመዘገበው መልካም የስራ አፈፃፀም ነው፡፡

በዋናነትም የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመንና ቀልጣፋ በማድረግ ረገድ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ 26 የአገልግሎት አይነቶችን ለተገልጋዮች ባሉበት ሆነው በኦንላይን አገልግሎትን ተደራሽ ማድረጉ ተጠቃሽ ነው፡፡  

በዚህም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በቅርቡ ባካሄደው ስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ 2024 በዲጂታል ዘርፍ ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው አገልግሎቶችን መጠቀም በማስቻል ረገድ  የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በምዝገባና ሰርተፍኬሽን አገልግሎት ተቋሙ ከ150 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ባለሙያዎች ስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች አገልግሎት ሰጥቷል፡፡

ተቋሙ ባለፉት አምስት አመታት 801 የመንግስት ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ የቁጥጥር ስራ አከናውኗል፡፡ በተለይም በዋጋ ግሽበት፣ በውል ብልሽት እና ተያያዥ በሆኑ ምክንያቶች ለበርካታ አመታት በጅምር ቀርተው የነበሩና የሀገር ሀብት የፈሰሰባቸው 758 የከፍተኛ ት/ት ተቋማት የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ተቋሙ ያካሄደው ጥናት ለመንግስት ውሳኔ በቀረበው መሰረት ማስተካከያዎች ተከናውነው ዳግም ወደ ግንባታ ከገቡት ውስጥ ከ500 በላይ የሆኑ ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ለሀገርና ለህዝብ ግልጋሎት እንዲበቁ ተደርጓል፡፡

Previous From Hamle/01/2015 E.C upto Tir/30/2016 E.C Registered and Renewed Companies(NEW REGISTERATION)

1 Comment

  • July 30, 2024

    ሁላችንም እንኳን ደስ ያለን።

Leave Your Comment

Bole, Addis Ababa,Ethiopia

Opening Hours:

Mon – Fri: 8:00 am – 6:00 pm

Calander

September 2024
M T W T F S S
 1
2345678
9101112131415
16171819202122
23242526272829
30  

ECA News & Updates

The latest Ethiopian Construction Authority news, articles, and resources, sent straight to your inbox every month.

Ethiopian Construction Authority © 2020. All Rights Reserved
Designed & Developed by Kanenus Technologies 0973200216