በ2016 በጀት አመት የተቋም ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ የሱፐርቪዥን ስራ ተካሄደ


ኢኮባ( ሐምሌ 21 ቀን 2015 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን አመራሮች የተቋሙን የ2016 በጀት አመት ዕቅድ፣ የቁጥጥር ስራ ማንዋሎች ዝግጅት፣ የቁጥጥር ስራ የሚከናወንባቸው የፕሮጀክቶች ልየታ እንዲሁም የተቋሙ የውስጥ አሰራር ዝግጅት ሂደት ላይ የሱፐርቪዝን ስራ አካሂደዋል፡፡


በዛሬው ዕለት በተካሄደው የሱፐርቪዥን ስራ ላይ የዕቅድ ዘመኑ የዝግጅት ምዕራፍ ላይ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የዕቅድና የቁጥጥር ስራ ማኑዋሎች እንዲሁም ቁጥጥር የሚካሄድባቸው የግንባታ ፕሮጀክቶች ልየታና የውስጥ አሰራር ዝግጅት ቡድን የሚያካሂዳቸው ተግባራት ይገኙባቸዋል፡፡ ዓላማውም በ2016 በጀት አመት በተቋሙ የሚከናወኑ ዕቅዶች በተናበበ እና በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀም የሚያስችል ተግባቦትን መፍጠር እንደሆነ ተመልክቷል፡፡


በዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ የተመሩት የተቋሙ አመራሮች የቡድኑን የእስካሁን የክንዋኔ ሂደት እና አፈፃፀም ግምገማ ያካሄደ ሲሆን፣ በፕሮግራሙ ላይ የንዑስ ቡድኖች በሂደቶቹ ላይ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡
ይህንኑ ተከትሎ በተገለፁት የሰነዶች ዝግጅት ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖች ላይ አወንታዊ ግብረመልሶች ተሰጥተዋል፡፡
ይበልጥ መጠናከር ባለባቸው፣ መሻሻል በሚገባቸው እንዲሁም በሚታከሉ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ውይይት ተካሂዷል፡፡


ኢንጅነር መስፍን ነገዎ አጠቃላይ ዝግጅቱን እንዲሁም ውይይቱንና ግብረመልሱን ተከትሎ መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫዎችን በማመላከት የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

የኢኮባ ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን

Previous የኢኮባ አመራሮችና ሰራተኞች የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ተወያዩ፡፡

Leave Your Comment

Connect With Us

Bole, Addis Ababa,Ethiopia

Mon – Fri: 8:00 am – 6:00 pm

Calander

December 2024
M T W T F S S
 1
2345678
9101112131415
16171819202122
23242526272829
3031  

Useful Links

ECA News & Updates

The latest Ethiopian Construction Authority news, articles, and resources, sent straight to your inbox every month.

Ethiopian Construction Authority © 2020. All Rights Reserved
Designed & Developed by Kanenus Technologies 0973200216